የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ለድሬደዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን የሳኒይዘር ድጋፍ አደረገ

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የኮረና ቫይረስ የወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል የሚረዳ ስልሳ ሁለት ሊትር (62 Ltrs) የሳኒታይዘር ድጋፍ ለድሬደዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን አስረክቧል፡፡ የተደረገውን ድጋፍ የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ተወካይ የሆኑት ረ/ፕሮፌሰር በላይ ስጦታው ለፖሊስ ኮሚሽን ተወካይ ለሆኑት ለኮማንደር ገመቹ ካቻ የተዘጋጀውን ሳኒታይዘር አስረክበዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው በቀጣይም ሳኒታይዘር በማምረት ለማህበረሰቡ ምርቱን ለማድረስ ድጋፉን በይበልጥ ማጠናከሩን ይቀጥላል፡፡


0

Active Students

0

Our Courses Programs

0

Our Teachers