የድሬዳዋ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መምህራንና ሰራተኞች ለአቅመ ደካሞች ህብረተሰብ ለምግብ ፍጆታዎች የሚሆን ድጋፍ አደረጉ

በአለም ደረጃ እንደ ወረርሽኝ የተከሰተውን የኮቪድ-19 ለመከላከልና ለመቆጣጠር በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በድሬዳዋ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት/ድ.ዳ.ቴ.ኢ/ በኩል ሰፊ ስራዎችን እየተከናወነ ይገኛል። ኢንስቲትዩቱ የበሽታውን ስርጭት ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚረዱ የንጽሕና መጠበቂያ /ሳንታይዘር/፣ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ፣ ከእጅ ንክኪ ነጻ የሆኑ የእጅ መታጠቢያ ማሽኖች እንዲሁም የእጅ መታጠቢያ ሳሙና፣ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እና ሌሎች ድጋፎችን ለህብረተሰቡ እያደረገ ይገኛል። በዛሬው ዕለትም የድ.ዳ.ቴ.ኢ ሰራተኞች ለህብረተሰቡ ድጋፍ እንዲያደርጉ በቀረበላቸው ጥያቄ መሠረት ከኪሳቸው ካዋጡት ከገንዘብ ውስጥ 35000/ሰላሳ አምስት ሺህ/ ብር በማውጣት የኢኮኖሚ ውስንነት ያለባቸው እና ዐይነ ስውራን ለሆኑ ሃያ አባወራዎች ባላቸው የቤተሰብ ብዛት መሠረት ለአንድ ወር የሚበቃ የተለያዩ የምግብ ፍጆታዎች የሚሆን ዘይት፣ ፓስታ፣ ሞኮሮኒ፣ ሩዝና ቲማቲም እንዲሁም በኢንስቲትዩቱ መምህራን የተዘጋጀ የንጽንህና መጠበቂያ ሳሙና እና የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭብል ድጋፍ ተደርጓል። ለዚህም በጎ ተግባር ለተሳተፉ አካላት በሙሉ የላቀ ምስጋናችንን እናቀርባለን። ኢንሰቲትዩቱ እንደዚህ ዓይነት ተመሳሳይ ስራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ለመግለጽ ይወዳል።
ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ
ሚያዚያ 28/2012 ዓ/ም

0

Active Students

0

Our Courses Programs

0

Our Teachers