የሥራ ቅጥር ብቃት ክህሎት እና የሥራ ዝግጅት ሥልጠና ( Employability Skill and Job Readiness) ለተመራቂ ተማሪዎች ተሰጠ

የሥራ ቅጥር ብቃት ክህሎት እና የሥራ ዝግጅት ሥልጠና ( Employability Skill and Job Readiness) ለተመራቂ ተማሪዎች ተሰጠ

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የሥራ ቅጥር ብቃት፣ ክህሎት እና የሥራ ዝግጅት ሥልጠና ለ2019 ዓ.ም. የአጋማሽ ዓመት ተመራቂ ተማሪዎች መስጠት ጀመረ። የሥልጠናው ዓላማ ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲ ወደ ሥራ ዓለም ሲቀላቀሉ የሚያስፈልጋቸውን የሥራ ፍለጋ፣ የራስ አቀራረብ፣ የሙያ እቅድ እና የግንኙነት ክህሎቶችን እንዲያዳብሩ ለማገዝ መሆኑ ተጠቁሟል።

ሥልጠናውን ያስጀመሩት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም እንደተናገሩት ተማሪዎች ስልጠናውን በአግባቡ በመከታተል በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው የቀሰሙትን እውቀት እና ክህሎት በተግባር እንዲያውሉ እንዲሁም በሥራው ዓለም አስፈላጊ የሆኑ መሰረታዊ ክህሎቶችን እንዲማሩ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በተጨማሪም የCEED ዳይሬክተር አቶ ካልኪዳን መዝገቡ ስለሥልጠናው ዓላማ፣ አስፈላጊነትና ከተማሪዎች የሚጠበቀውን ተሳትፎ አስመልክተው ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ሥልጠናው በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የስራ ዕድል ፈጠራ ልማት ማዕከል (CEED) ከተለያዩ ኮሌጆች ጋር በማስተባበር የተዘጋጀ ሲሆን፣ የማመልከቻ ደብዳቤ አጻጻፍ፣ የCV ዝግጅት፣ የቃለ መጠይቅ ዝግጅት፣ የሙያ ጎዳና ልማት እና የኔትወርክ ግንኙነት ክህሎት ላይ ያተኮረ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

Recent News