ትምህርት ሚኒስቴር ልዩ የአዳሪ ትምህርት ቤቶችን በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ያቋቋመ ሲሆን በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገነባው አዳሪ ትምህርት ቤት ተገንብቶ እስኪጠናቀቅ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በጊዜያዊነት ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ለሚመጡት ባለ ልዩ ተሰጥኦ የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች የሚሆን ልዩ የመማሪያ ክፍሎች፣ የማደሪያ ስፍራ፣ ቤተመፅሐፍት፣ የህክምና መስጫ ማዕከል እና ሌሎች አስፈላጊ ግብዓቶችን በማሟላት ተማሪዎችን መቀበል ጀምሯል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በ2019 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ከተለያዩ ክልሎች የተውጣጡ 183 ወንድ እና 61 ሴት በድምሩ 244 ባለ ልዩ ተሰጥኦ የ9ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ እንደሚያስተምር ለማወቅ ተችሏል፡፡
ድሬዳዋ፣ መስከረም 19፣ 2019 (የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት)





