
በድሬዳዋ ከተማ የሚገነባው የፌደራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ተገንብቶ እስኪጠናቀቅ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከሁሉም የሀገሪቱ አካባቢዎች የተውጣጡ 193 የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ጀምሯል፡፡
የመማር ማስተማር ስራው እንዲጀመር የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሰፊ ዝግጅት ሲያደርግ የቆየ ሲሆን ለተማሪዎች ምቹ የመማሪ ክፍሎች፣ የማደሪያ ቦታ፣ የመጀመሪያ ደረጃ ህክምና፣ መመገቢያ እና ማንበቢያ ስፍራዎችን በማዘጋጀት ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ጀምሯል፡፡





