


በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በ2019 ዓ.ም አዲስ የተመደባችሁ መደበኛ ተማሪዎች እና በ2018 ዓ/ም በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ትምህርታችሁን ስትከታተሉ ቆይታችሁ የማለፊያ ውጤት ያመጣችሁ ተማሪዎች በሙሉ
የ2019 ዓ/ም ትምህርት ዘመን በአካል በመገኘት ሪፖርት ማድረጊያ ቀን ጥቅምት 07 እና 8/2019 ዓ/ም እንዲሁም ገለፃ የሚሰጠው ጥቅምት 9 ቀን 2019 ዓ/ም መሆኑን እንገልፃለን :፡
ተማሪዎች ለምዝገባ ስትመጡ፦
ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
የ12ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
አራት 3×4 መጠን የሆኑ ጉርድ ፎቶግራፎች፣
National ID Fayda
አንሶላ፣ የለሊት ልብስ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ልብስ።
ከተጠቀሱት ቀናት ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪን የማናስተናግድ መሆኑን እናሳዉቃለን
ማሳሰቢያ፡
በተለያዩ ምክንያት 1ኛ ዓመት 1ኛ ወሰነ ትምህርት ትምህርታችሁን አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ የሚያበቃ ውጤት ያላችሁ እና የመልሶ ቅበላ ፎርም የሞላችሁ ተማሪዎች ለመልሶ ቅበላ ጥቅምት 10 እና 11 ቀን 2019 ዓ.ም ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
=================
