ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ከ500 በላይ የፍራፍሬ ችግኞችን ተከለ፣ ዩኒቨርሲቲው የአካባቢ ጥበቃ እና የአረንጓዴ ልማት ሥራዎችን በትኩረት የሚሰራ ኮሚቴ በማቋቋም እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ከ500 በላይ የፍራፍሬ ችግኞችን ተከለ፣ ዩኒቨርሲቲው የአካባቢ ጥበቃ እና የአረንጓዴ ልማት ሥራዎችን በትኩረት የሚሰራ ኮሚቴ በማቋቋም እንቅስቃሴ ጀምሯል፡፡

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ «ለነገ አረንጓዴ ሽፋን ዛሬ ችግኞችን እንትከል» በሚል መሪ ቃል ከ500 በላይ የተለያዩ የፍራፍሬ ችግኞችን ተክለዋል።
በሚያዝያ ወር 2018 ዓ.ም የተቋቋመው የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ «Climate Action Committee» የዓመታዊ ዕቅዱ አካል አድርጎ ከቀረጻቸው ዋና ዋና ተግባራት መካከል የጊቢውን አረንጓዴነት ማሳደግ (Campus Greenery) አንዱ እንደሆነ ይታወቃል። የዛሬው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብርም ይህንኑ ዕቅድ ወደ ተግባር ለማውረድ ከተከናወኑ የልማት ሥራዎች አንዱ ነው።
በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ ላይ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም፣ የአስተዳደር እና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሰለሞን ዘሪሁን፣ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ግርማ ቤካን ጨምሮ መካከለኛ እና ከፍተኛ አመራሮች፣ መምህራን እንዲሁም የኮሚቴው አባላትና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ የነቃ ተሳትፎ አድርገዋል።
ኮሚቴው በቀጣይም የአካባቢ ጥበቃ እና የአረንጓዴ ልማት ሥራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ታውቋል።

Recent News