Logo
News Photo

የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ የ2015 ዓ.ም የበጋ ስቴም (STEM) ሰልጣኝ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና ሰጠ።

እንደሚታወቀው የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ስቴም ማዕከል (STEM Center) በድሬዳዋ አስተዳደር ስር ከሚገኙ የ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በሳይንስ (ፊዚክስ፤ ባዮሎጂና ኬሚስትሪ) እና ሒሳብ የትምህርት ዓይነቶች የተሻለ ውጤት ያላቸውን ተማሪዎች በመመልመል በተግባር የተደገፈ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ስልጠና የሚሰጥ ማዕከል ነው፡፡

በመሆኑም ማዕከሉ የ2015 ዓ.ም የበጋ ስቴም ስልጠና  መርሀ-ግብርን ለመጀመር በአስተዳደሩ ከሚገኙ የመንግስትና የግል ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ ቁጥራቸው ከ400 (አራት መቶ) በላይ ለሆኑ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና የሰጠ ሲሆን በቀጣይ ዩኒቨርሲቲው ባለው የመቀበል አቅም መሰረት የማለፊያ ውጤቱን ላመጡ ተማሪዎች ሥልጠናውን በያዝነው ወር አጋማሽ እንደሚጀምር ታውቋል፡፡

ማዕከሉ የስቴም የበጋ መርሀ-ግብር ስልጠናውን የሚሰጠው በሳምንቱ መጨረሻ ቅዳሜ እና እሁድ ሲሆን ከስልጠና በተጨማሪ የተለየ የፈጠራ ችሎታ ያላቸውን ተማሪዎች በማወዳደር አሸናፊ ለሆኑ ተማሪዎች የፈጠራ ሃሳባቸውን ወደ ተግባር የሚቀይሩበትን ሁኔታ ዩኒቨርሲቲው እንደሚያመቻችላቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡

Share This News

Comment