Logo
News Photo

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቴከኖሎጂ ኢንስቲትዩት መምህራን ተሰርተው ለተጠናቀቁ የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎች Validation Workshop አካሄደ።

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቴከኖሎጂ ኢንስቲትዩት በስሩ በሚገኙ መምህራኖቹ ተሰርተው ለተጠናቀቁ የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎች Validation Workshop አካሂዷል።
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በስሩ በሚገኙ መምህራኖቹ በተለያዩ የት/ት መስኮች ለማህበረሰቡ ችግር ፈቺ ጥናት እና ምርምሮች እንዲሁም የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎችን እያከናወነ ሲሆን ከእነዚህ ስራዎች መካከል በስሩ በሚገኙ እና ከተለያዩ የት/ት መስኮች በተወጣጡ መምህራኑ ሲስሩ ቆይተው የተጠናቀቁ በሶፍትዌር ማበልጸግ ፣ መካኒካል ማንፋክቸሪንግ እና ኤሌክትሪሲቲ ላይ ያተኮሩ በአጠቃላይ 3 ሶፍትዌሮች እንዲሁም 4 ኤሌክትሮ ሜካኒካል በድምሩ 7 የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎች በዛሬው እለት የውስጥ እና የውጪ ተጋባዥ ባለድርሻ አካላቶች በተገኙበት Validation Workshop አካሂዷል፡፡
በፕሮግራሙ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደርጉት የኢንስቲትዩቱ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ተወካይ እንዲሁም የኢንስቲትዩቱ ምክትል ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አማን ሁሴን በኢንስቲትዩቱ ስራ ያሉትን የት/ት ፕሮግራሞች እንዲሁም የተማሪ እና የመምህራኑ ቁጥር ለፕሮግራሙ ታዳሚዎች ገለፃ ካደረጉ በኋላ ከመማር ማስተማሩ ባለፈ በዛሬው እለት እነዚህ መምህራን ካለባቸው የመማር ማስተማር እና የኃላፊነት ቦታዎችን ከመምራት ባላፈ ጊዚያቸውን ለጎን የማህበረሰቡ ችግር ለመፍታት የሚያስችሉ ተጫባጭ የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎች ላይ ተሳትፈው ማጠናቀቃቸው እጅግ የሚያስደንቅ እና የሚያስደስት መሆኑን በመግለጽ ለሌሎች መምህራን ተሞክሮ መሆን የሚያስችል ስራዎችን መስራታቸው በኢንስቲትዩቱ ስም ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
በመቀጠልም የኢንስቲትዩቱ የምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ቢሮ ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ግርማ ቤካ በዛሬው እለት ቴክኖሎጂ ሽግግር ስራቸውን ያጠናቀቁ መምህራን የቴክኖሎጂ ስራዎቹ ተጀምረው እስክጠናቀቁ ያጋጠሟቸውን ችግሮች እና ተግዳሮቶች ሳይበገሩ ተቋቁመው ለዚህ ማጠናቀቅ ደረጃ በመብቃታቸው እጅግ ሊመሰገኑ የሚገባ መሆኑን የገለፁ ሲሆን እነዚሁ መምህራኑ በቀጣይ የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎቹ ለማኅበረሰቡ ለማስተላልፍ በሚደረገው ሂደት ላይ ከኢንስቲትዩቱ ጋር ባለድርሻ አካላት ሆነው እና ቴክኖሎጂ ሽግግሮቹ የሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመሆን አሁንም ተመሳሳይ ጥረት እንዲያደርጉ እንዲሁም ሌሎች መምህራንም የእነዚሁኑ መምህራን ተሞክሮ እንዲወስዱ እና አዳዲስ ሀሳቦችን በማምጣት እንዲሰሩ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በመጨረሻም የኢንስቲትዩቱ የቴክኖሎጂ ሽግግር እና ኢንስቲትዩት ኢንዱስትሪ ቁርኝት ቢሮ ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ አባይነህ እንደገለፁት ዛሬ ላይ ተጠናቀው ከቀረቡት የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎች በተጨማሪ በያዝነው በጀት ዓመትም መጨረሻ ሊያዘገዩ የሚችሉ ሁኔታዎች ካልተፈጠሩ በስተቀር ሌሎች ተጨማሪ በመሰራት እና በሂደት ላይ ያሉ የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎች እንደሚኖር እንዲሁም እንደዛሬው በተመሳሳይ መልኩ ለእይታ እንደሚቀርቡ ከፕሮግራሙ መጠናቀቅ በኋላ ለዩኒቨርሲቲው ህዝብ ግንኙነት በሰጡት ቃለ-መጠይቅ ላይ አመልክተዋል፡፡

Share This News

Comment