Logo
News Photo

እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን !!

ድሬ ዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከመምህራኖቹ ጋር በዛሬው ቀን ሚያዝያ 16 ቀን 2015 ዓ.ም ከኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን በቅጅና በተዛማጅ መብቶች የሚያስገኙ ስራዎች  ሶስት የምዝገባ የምስክር ወረቀት አገኘ፡፡ 

የዩኒቨርሲቲያችን መምህራንና ተመራማሪ በሆኑት ዶ/ር ጋዲሳ ኦላኒ፣ መ/ር አንድነት አሰፋ፣  መ/ር ዳመና ደስታ እና መ/ር ጌትነት ቶሎሳ እንደ ሀገር የመጀመሪ የሆኑ ሁለት ስራዎችን ማለትም “የጦር መሳሪያዎች መመዝገቢያ ማስተዳደሪያ ሲስተም ሶፍትዌር (FARS)“  እና “የተቀናጀ የእንግዶች አስተዳደር ሲስተም ሶፍትዌር (IGMS)“ እንዲሁም   መ/ር አንድነት አሰፋ፣  ዶ/ር ጋዲሳ ኦላኒ እና መ/ር ዳመና ደስታ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጠውን የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና በተሻለ ደረጃ ለማስተዳደር ፣ ለመምራት ፣ ተማሪዎችን በማገዝ እና ሌሎች ዘርፈ ብዙ ጥቅሞችን የያዘ “የመፈተኛና የማስተማሪያ መረጃ ማደራጂያና ማስተዳደሪያ ሲስተም ሶፍትዌር (GOBEZ+)“ ከአእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን በቅጅና በተዛማጅ መብቶች  የሚያስገኙ ስራዎች  ሶስት የምዝገባ የምስክር ወረቀት አገኘ፡፡

የኒቨርሲቲያችን ይህን ጨምሮ በዚህ በጀት ዓመት በአጠቃላይ አራት የምዝገባ ምስክር ወረቀቶችን ያገኘ ሲሆን መምህራን በሚሰሯቸውን መሰል ስራዎችን ለማገዝ ከምንጊዜውም በላይ ቁርጠኛ መሆኑን ለማሳወቅ ይወዳል፡፡

በድጋሜ መምህራኖቻችንና የዩኒቨርስቲውን ማህበረሰብ እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን፡፡

Share This News

Comment