የዩኒቨርሲቲው የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ባዘጋጀው ስልጠና ላይ በተለያየ የስራ ኃላፊነት ላይ የሚገኙ የአስተዳደር ሠራተኞች በስልጠናው ተካፋይ ሆነውበታል፡፡
ለአንድ ቀን በቆየው ስልጣና በዋነኝነት የጥቅም ግጭት ፅንሰ ሃሳብን አስመልክቶ የተሰጠ መሆኑን የገለፁት ስልጠናውን የሰጡት የህግ ኮሌጅ መምህሩ ረ/ፕ እንዳወቅ ፀጋው ናቸው፡፡
እንደ ረ/ፕ እንዳወቅ ገለፃ ከሆነ በስልጠናው የጥቅም ግጭት ምንነት፣ አይነቶቹ፣ መንስዔው እና የሚያስከትላቸው ጉዳቶቹ ላይ በዝርዝር ገለፃ ተደርጎባቸው ሠራተኛው በቂ ግንዛቤ እንዲያገኝ መደረጉን ተናግረዋል፡፡
ከስልጠናው መጠናቀቅ በኋላም አንዳንድ የአስተዳደር ሠራተኞች እንደገለጹት ስልጠናው ለጥቅም ግጭት አጋላጭ የሆኑ አሠራሮችን አስቀድመው መለየት የሚችሉብትን ግንዛቤ እንዲያገኙ አድርጓቸዋል፡፡
በዚህም ካለው ነባራዊና ተጨባጭ ሁኔታ ተነስተው በተቋማቸው ውስጥ የጥቅም ግጭትን አስቀድመው መከላከል የሚችሉብት አቅም የፈጠረላቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡
Dire Dawa University is found in the industrial and commercial city of Dire Dawa, which is located at 515 km east of Addis Ababa. It is a young higher education institution, established and started its teaching and learning activities in 2007 academic year.
Copyright © 2021, Dire Dawa University. All Rights Reserved.
Share This News