Logo
News Photo

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የበለፀገው የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ማረሚያ፣ ውጤት ማደራጃ እና ማስተዳደሪያ ሶፍትዌር አገልግሎት ጀመረ፡፡

ሶፍትዌሩ እንደ አስተዳደር የትምህርት ስርዓቱን ለማዘመን በሚደረገው ጥረት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት ክቡር ከንቲባ ከድር አስታውቀዋል።

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ዘርፉን በቴክኖሎጂ ለማዘመን እያደረገ ለሚገኘው ከፍተኛ ጥረት እና ድጋፍ የአስተዳደሩ ስም አመስግነዋል።

በ2017 ድሬዳዋን የዘመነች ከተማ (Smart City) ለማድረግ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በትብብር ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡

ክቡር ከንቲባ ከድር ጁሀር 7 ሺህ ለሚጠጉ የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች እንዲሁም 9 ሺህ ለሚሆኑ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች መለያ ቁጥር በመስጠት ሶፍትዌሩን በይፋ ስራ አስጀምረዋል።

Share This News

Comment