Logo
News Photo

ዩኒቨርሲቲው ስርዓተ ትምህርቶችን ከኢንዱስትሪዎች ፍላጎት ጋር ለማጣጣም እያደረገ ያለው ጥረት ሊደነቅ እነደሚገባ ተጠቆመ

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞችን ስርዓተ ትምህርት የመከለስ ስራ በስፋት እያከናወነ ሲሆን በህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የማስተርስ ዲግሪ በህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ (Master of Public Health) እንዲሁም በቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ Logistics and Supply Chain Management የስርዓተ ትምህርት ክለሳ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጡ ምሁራን እና የኢንዱስትሪ ባለሙያዎች አማካኝነት ተደርጓል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም በዚሁ መርሃ ግብር ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት ዩኒቨርሲቲው የአፕልይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ እንደመሆኑ መጠን የተሰጠውን ተልኮ ለማሳካት የስርዓተ ትምህርት ክለሳ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አመልክተዋል፡፡ ዶ/ር መገርሳ ቃሲም አያይዘውም ገምጋሚዎች የሚሰጡት አስተያየት ትምህርት ሚኒስተር ያስቀመጠውን የተግባር ተኮር ዩኒቨርሲቲ ልየታን መሰረት ያደረግ መሆን እንዳለበት ጠቁመዋል፡፡

የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ሁሴን መሀመድ በብኩላቸው ኮሌጁ ብቁ እና ተወዳዳሪ ምሩቃንን ለማፍራት ውጤት ተኮር የስርዓተ ትምህርት ክለሳ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ከውጭ የተጋበዙ ምሁራን እና የኢንዱስትሪ ባለሙያዎች በሰጡት አስተያየት በእለቱ የተከለሱት ስርዓተ ትምህርቶች የትምህርት ሚኒስቴር ባስቀመጠው የክለሳ ሂደት መሰረት መዘጋጀታቸውን ገልፀው ዩኒቨርሲቲው ስርዓተ ትምህርቶችን ከኢንዱስትሪዎች ፍላጎት ጋር ለማጣጣም እያደረገ ያለውን ጥረት አድንቀዋል፡፡

Share This News

Comment