Logo
News Photo

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የሎጅስቲክና ሰፕላይ ቼይን ማኔጅመንት የትምህርት ክፍል ሎጅስቲክና አመራርነትን አስመልክቶ ለድሬደዋ ጉምሩክ ኮምሽን ቅ/ጽ ቤት ሠራተኞች ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡

በስልጠናው መክፈቻ ላይ ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣቹህ ንግግር ያደረጉት በዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሰለሞን ዘሪሁን እንዳሉት የመንግስት ገቢ አሰባሰብን በማዘመን የተገኘውን ገቢ በማሳደግ በሀገራችን እድገት እንዲመዘገብ በዘርፉ ላይ የሚሰሩ ባላሞያዎቸን ወቅቱ ከሚጠይቀው ቴክኖሎጂ ጋር ማስተዋወቅ እና አቅማቸውንም በየጊዜው ማጎልበት  ያስፈልጋል፡፡

ለዚህ ደግሞ ባለሞያው በየጊዜው ተከታታይነት ያላውን ስልጠና እንዲወስድ በማድረግ  አቅሙን  በመገንባት ብቁና በተለያዩ ክህሎቶች የዳበረ ባለሞያ እንዲሆን  ማድረግ ያስፈላጋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ ደመላሽ ተሾመ በዚሁ ስልጠና መክፈቻ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልእክት የስልጠናው ተሳታፊ የቅ/ጽ ቤቱ ሠራተኞች ስልጠናውን በትኩረት ተከታትለው የሚቀስሙትን እውቀት ተጠቅመው ለደንበኞቻቸው ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግልትን በመስጠት ኮምሽኑ የሰነቀውን ርዕይ ማሳካት እንዲችል የተጣለባቸውን ኃላፊነት መወጣት ይኖርባቸዋል ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡

ለ4 ተከታታይ ቀን በሚቆየው ስልጠና ላይ ቁጥራቸው 60 የሚደርሱ የድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ ቤት ሠራተኞች በሁለት ዙር ስልጠናው እንደሚሰጣቸው ከስልጠናው አስተባባሪዎች ለማወቅ ተችሏል፡፡

Share This News

Comment