ለ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች በነገው እለት መውሰድ የሚጀምሩትን ፈተና አስመልክቶ ገለፃ ተደረገላቸው፡፡
በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በዘንድሮ ዓመት ከ11 ሺህ በላይ የማኅበራዊና ተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተናቸውን ለመውሰድ ተመድበዋል፡፡
ዛሬ ከሰአት ላይ ለመጀመሪያው ዙር የማኅብዊ ሳይንስ ተማሪዎች በነገው እለት የሚወስዱትን ፈተና አስመልክቶ በተደረገው ገለፃ ላይ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም ተማሪዎቹን እንኳን ደህና መጣቹህ በማለት መልዕከታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ዶ/ር ኡባህ በመልዕክታቸው ተማሪዎች ከኩረጃ በፀዳ በዕውቀታቸው ብቻ የተዘጋጀላቸውን ፈተና በመሥራት የጥረታቸው ውጤት የሆነውን ለማግኘት መጣር ይገባቸዋል ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡
በዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው ተፈታኝ ተማሪዎች ምንም አይነት ችግር እንዳይገጥማቸው በቂ ዝግጅት ሲደረግ መቆየቱን ጠቁመው ተማሪዎችም የፈተናውንና የግቢውን ህግ በማክብር የፈተናው መርሀግብር በስኬት እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡
ለማኅበራዊ ሳይንስ የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከትምህርት ሚኒስቴር በመጡ የፈተና አስተባባሪዎች እንዲሁም ከፈተናው አሰጣጥ ጋር ጠቃሚነት ያላቸው መልዕክቶን አስመልክቶ ገለፃ ተደርጓል፡፡
በወረቀት ፈተናውን ለሚወስዱት ተማሪዎች ከተደረገው ገለፃ በተመሳሳይ በበይነ መረብ ፈተናቸውን ለሚወስዱ ተማሪዎችም የፈተና አሰጣጡ ላይ እና ተማሪዎች በፈተናው ሂደት መከተል የሚገባባውን ሂደቶች ላይ ከትምህርት ሚኒስቴር በመጡ የበይነ መረብ ፈተና አስተባባሪዎች እና በኒቨርሲቲው አይሲቲ ዳይሬክቶሬት ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡
Share This News