Logo
News Photo

ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ዋለ

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዲሁም ከድሬደዋ አስተዳደር ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ጋር በመተባበር ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን (March በደማቅ ሁኔታ አክብሯል፡፡

"50 ዓመት የሴቶችን ድምፅ ለእኩልነትና ለበለፀገች ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ቃል በተከበረው በዓል ላይ የብልፅግና ፓርቲ ህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ ፈዲላ ቢያ፣ የድሬዳዋ አሰተዳደር ገንዘብና ኤኮኖሚ ልማት ቢሮ ሃላፊ እና የከንቲባ ተወካይ የሆኑት / ሙሉካ መሃመድ፣ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር እና የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ተወካይ / ግርማ ቤካ፣ በሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የህጻናት ጉዳይ መምሪያ ሃላፊ ተገኝተዋል፡፡

ለዓሉ ታዳሚዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር እና የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ተወካይ / ግርማ ቤካ ‘’ሴቶች የተለያዩ ተግዳሮቶችን ተቋቁመው በሁሉም የስራ ዘርፎች ስኬታማ መሆን ከመቻላቸውም በላይ ለሀገር እድገት እና ብልጽግና የማይተካ ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ’’ ብለዋል፡፡

የዘንድሮው ክብረ በዓል በአራት ዋና ዋና ምሰሶዎች ማለትም የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት፣ አመራርነት፣ ጥቃትን መከላከል እና ቴክኖሎጂ ላይ ያተኮረ ነው ያሉት / ግርማ አክለውም ‘’የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በበሴት ፕሬዝዳንት አመራር ሰጪነት እየተመራ በርካታ ተቋማዊ ለውጦችን ማስመዝገብ የቻለ ሴቶች በመሪነት ቦታ ላይ ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት እንደሚችሉ ያሳየ ህያው ምስክር ነው‘’ ብለዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው የሴቶችን ተሳትፎ የሚያረጋግጡ በርካታ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ጠቁመው በቀጣይነትም የሴት ምሁራንን አቅም ከማሻሻል እንጻር ሰፊ ስራዎችን እንደሚሰራ ጠቁመዋል፡፡

በመድረኩ ላይ የብልፅግና ፓርቲ ህዝብና አለም ዓቀፍ ግንኙነት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ፈዲላ ቢያ እንደተናገሩት ማርች 8 ሴቶች በኢኮኖሚው፣ በሳይንስ እና በቴክኖሎጂ ዘርፍ ላይ እውቀትን፣ ክህሎትን አዳዲስ ግኝቶችን ለአለም በተግባር ያሳዩበትን ቀን የሚዘክር ነው፡፡ የሀገራችን ሴቶች የአሁኑን ትውልድ እውቀት በመቅረፅ እና የቀጣይ ትውለድን ራዕይ በማመላከት ፋና ወጊ መሆናቸውን በንግግራቸው የጠቆሙት ሚንስትር ዲኤታዋ ሴቶች በተለይ ሴት ምሁራን እና አመራሮች እርስ በእርስ በመደጋገፍ እና በመረዳዳት ለሀገር እድገት እና ብልጽግና የድርሻችንን ልንወጣ ይገባል ብለዋል፡፡

በእለቱ የኢትዮጵያ ሴት ሙሁራንን ሚና በሚመለከት / ህሊና አሸናፊ እንዲሁም 50 አመት የለውጥ ጉዞና ማርች 8 አከባበርን አስመልክቶ / እማዋይሽ ተገኝ የመወያያ ሰነድ አቅርበው ከበዓሉ ተሳታፊዎች ጋር ውይይት ተደርጎበታል፡፡

ዓለም አቀፉን የሴቶች ቀን እንዲሁም 50 ዓመት የለውጥ ጉዞ አስመልክቶ የሻማ ማብራት፣ የዳቦ እና ኬክ ቆረሳ መርሃ ግብሮችም በቅደም ተከተል ተካሂደዋል፡፡

 

Share This News

Comment