Logo
News Photo

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ያመረታቸውን ዘመናዊ የምግብ ማብሰያ ምድጃዎች ለአስተዳደሩ ግብርና፣ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ አስረከበ

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ያመረታቸውን ዘመናዊ የሮኬት ስቶቭ የምግብ ማብሰያ ምድጃዎችን ለድሬዳዋ ግብርና፤ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ያስረከበ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው ወደ ተግብር ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ እያደረገ ያለውን ስትራቴጂካዊ ሽግግር ያመላከተ  ስራ ሆኗል፡፡

ፕሮጀክቱ ዩኒቨርሲቲው በቋሚነት ከሚሰራቸው የቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎቹ አንዱ ከመሆኑም ባሻገር ሀገራችን ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም ማህበረሰብ ለመገንባት እንዲሁም አረንጓዴ ኢኮኖሚን ለመገንባት የጀመረችውን ጥረት የሚደግፍ ስለመሆኑ ተመላክቷል። 

ዩኒቨርሲቲው ሰርቶ ያጠናቀቀው ስራ ለምግብ ማብሰል የሚጠፋውን ከፍተኛ የእንጨት ፍጆታ የሚቀንስ ሲሆን የደን ምንጣሮን ለሚከላከልና እንዲሁም የካርቦን ልቀትን (Carbon Emission) በመቀነስ ረገድ የሚጫወተው ሚና የላቀ ነው፡፡ 

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ሳይንትፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ግርማ ቤካ ይህንኑ  በማስመልከት እንደተናገሩት ኢንስቲትዩቱ የድሬዳዋንና የአካባቢውን ችግሮች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እና ዘመናዊ አሰራሮችን በማስተዋወቅ ለመፍታት የጀመረውን ቁርጠኝነት ያሳየበት  ስራ መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይም የዩኒቨርሲቲ-ኢንዱስትሪ ትስስርን በማጠናከር የማህበረሰቡን ችግር የሚፈቱ ለሎች አማራጭ ተክኖሎጂዎችን በማስፋፋት ረገድ ይሰራል ብለዋል፡፡ 

ፕሮጀክቱ በድሬዳዋ አስተዳደር ግብርና፣ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ የምግብ ስርዓት የመቋቋም አቅም ግንባታ (FSRP) ፕሮጀክት የገንዘብ ድጋፍ የተከናወነ ሲሆን በቀጣይም  ሀይል ቆጣቢ እና ዘመናዊ የምግብ ማብሰያ ምድጃዎችን ለመስራት

Share This News

Comment