የከተማ ፕላን፣ መሬት እና የከተማ ፋይናንስን በተመለከተ ከከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጋር በመተባበር ሲሰጥ የቆየ ስልጠና ተጠናቀቀ
ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የከተሞች ገቢ ሪፎርም ፕሮጀክት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ሲሰጥ የቆየው የከተማ ፕላን፣ መሬት እና የከተማ ፋይናነስ ዘርፍ ሥልጠና እና የብቃት ማረጋገጫ ምዘና ፕሮጀክት ማጠቃለያ መርሀግብር ተካሄደ።
በስልጠናው ከአፋር፣ ከሶማሌ እና ከሀረሪ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንዲሁም ከድሬዳዋ አስተደዳር የተውጣጡ 140 የዘርፉ ባለሞያዎች የተሳተፉ ሲሆን ሰልጣኞች በቴክኖሎጂ የተደገፈ የተግባር እና የንድፈ ሀሳብ ስልጠና እንዲያገኙ መደረጉም ተጠቁሟል፡፡
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም በመዝጊያ መርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት ‘’ስልጠናው የከተማ ፕላን እና የመሬት አስተዳደር፣ የካዳስተር ምዝገባ ሥርዓት ፣ መሬትና ንብረት ግመታ የሚታዩ ችግሮችን በመቅረፍ ግልጽ የመሬት አስተዳደር፣ የተቀላጠፈ የከተማ ዕድገት እና ጠንካራ ተቋማዊ አፈጻጸም እንዲሰፍን የሚያስችል ነው’’ ሲሉ ተናግረዋል፡፡
በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር የከተሞች ገቢ ሪፎርም ፕሮጅክት ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ የሆኑት ወ/ሮ ዚነት ኢብራሂም በበኩላቸው የከተሞች ልማት ለሀገር ኢኮኖሚ የማይተካ ሚና እንዳላቸው የገለፁ ሲሆን በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን የተሰጠው ስልጠና የከተማ መሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ስርዓትን በማዘመን ከመሬት አስተዳደር ጋር ተያይዞ የሚታዩ ችግሮችን መቅረፍ ያስች ብለዋል፡፡
የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ ባለሞያዎችን በማሰልጠን ብቁ የመሬት አስተዳደር ባለሙያዎችን ማብቃት የቻለ ሲሆን በዚህኛው ዙር 140 ባለሙያዎችን አሰልጥኖ የብቃት ማረጋገጫ ስልጠና ዝግጁ ማድረጉ ተገልጿል፡፡
Share This News