Logo
News Photo

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እምርታ ቤተ- መጽሐፍን የማደራጀት ስራ እየሰራ መሆኑ ተገለፀ

የድሬዳዋ አስተዳደር ከጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ የ ‘’መደመር’’ መፅሐፍ ሽያጭ በተገኘ ገቢ የሚያሰራው የ ‘’እምርታ’’ ቤተ-መጽሐፍ ግንባታ ተጠናቆ ከፊል አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ይታወቃል፡፡ ቤተ-መጽሐፉን የማደራጀት እና ለአገልግሎት ዝግጁ የማድረግ ስራን ደግሞ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከአስተዳደሩ ጋር በመተባበር እየሰራ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቤተ-መጽሐፍት ዳይሬክቶሬት እንዲሁም የዩኒቨርሲው ICT ዳይሬክቶሬት ‘’እምርታ’’ ቤተ መጽሐፍትን የማደራጀት፣ ዲጂታል አማራጮችን የማስተዋወቅ እና ቤተ መጽሐፉን ለ አገልግሎት ዝግጁ የማድረግ ስራ በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ዩኒቨርሲቲው ለእምርታ ቤተ-መጽሐፍት የመጽሐፍት ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በተለያየ መንገድ የተሰባሰቡ መጽሐፍቶችን ለአንባቢ ምቹ በሆነ መንግድ የማደራጀት፣ የሼልፍ እና ማንበቢያ ቦታ ዝግጅት ስራዎችን የተቋሙን ባለሙያዎች በመመደብ እየሰራ ይገኛል፡፡ 

ዘመናዊ ቤተ-መጽሐፍት ሊያሟላ የሚገባውን የዲጂታል መጽሐፍት እና የዲጂታል መጽሐፍት ቋት ዝግጀትም በዩኒቨርሲቲው የ ICT ባለሙያዎች ተሰርቷል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ከዚህ ባሻገር የኢንተርኔት ዝርጋታ ስራ የሚውሉ ቁሳቁሶችን እና የኮምፒተር ኔትወርኪንግ ስራዎችን ለ ‘’እምርታ’’ ቤተ መጽሐፍት ድጋፍ አድርጓል፡፡

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የአካባቢውን ማህበረሰብ ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ የማህበረሰብ ጉድኝት እና የማህበረሰብ አገልገሎት ስራዎችን በመስራት ላይ የሚገኝ ሲሆን የተቋማትን አገልግሎት የሚያዘምኑ እና ነባራዊ ችግሮቻቸውን መፍታት የሚያስችሉ ምርምሮችን በመስራት እንዲሁም በተለያዩ ሰብዓዊ እና ሀገራዊ ጉዳዩች ላይ ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ከመንግስት እና ህዝብ የተሰጠውን ተልዕኮ በመወጣት ላይ እንደሚገኝ ተመላክቷል፡፡

Share This News

Comment