የሦስተኛው ሩብ ዓመት እቅድ ክንውን ሪፓርት እና የ9 ወራት ጥቅል አፈጻጸም ለዩኒቨርሲቲው ካውንስል ቀርቦ ተገመገመ
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤቶች የ2018
በጀት ዓመት የሦስተኛ ሩብ ዓመት እቅድ ክንውን ሪፓርት እና የ9 ወራት ጥቅል አፈጻጸም ሪፓርት ለዩኒቨርሲቲው ካውንስል አባላት አቅርበዋል፡፡ የቀረበውን ሪፓርት ተከትሎም ግመገማዊ ግብረ መልስ እና ውይይት ተደርጓል፡፡
ቢሮዎቹ በሩብ ዓመቱ የሰሯቸውን ስራዎች በ4 ግቦች እና በርካታ ዝርዝር ተግባራት ከፋፍለው ያቀረቡ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው ቁልፍ ውጤት አመላካቾችን መሰረት አድርጎ የተገኙ ውጤቶች፣ ከፍተኛ እና ዝቅተኛ አፈጻጸም የታየባቸው ተግባራት፣ በሩብ ዓመቱ የተስተዋሉ ተግዳሮቶች እና የተወሰዱ እርምጃዎችን በዝርዝር አቅርበዋል፡፡
ሁሉም ሪፓርቶች በገምጋሚዎች እና በካውንስል አባላት ግብረ መልስ የተሰጣቸው ሲሆን ግብረ መልሶቹን ተከትሎ ማብራሪያ በሚፈልጉ ጉዳዮች ላይ ቢሮዎቹ ምላሽ እንዲሰጡ ተደርጓል፡፡
በቀጣይ በጅምር ያሉ እና መጠናቀቅ የሚገባቸው ስራዎችን የሚጠናቀቁበት፣ ደካማ አፈጻጸም በታየባቸው ተግባራት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰራበት እንዲሁም የ2019 በጀት ዓመት ዝግጅት መዕራፍ የሚጀመርበት እንደመሆኑ በየደረጃው የሚገኙ የዩኒቨርሲቲው የስራ ክፍሎች ርብርብ ማድረግ እንደሚገባቸው ተጠቁሟል፡፡
Share This News