የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል ያለመ የሥነ-ልቦና ስልጠና ተሰጠ
የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የሥነ-ልቦና ትምህርት ክፍል ጋር በመተባበር ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች "የአስተሳሰብ ለውጥ" (Mindset) ስልጠና ሰጠ። በአዲሱ ሁለተኛ ደረጃ እና በአፈተኢሳ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለሚገኙ ተማሪዎች የተዘጋጀው ይህ ስልጠና፤ ተማሪዎች ለብሔራዊ ፈተና ያላቸውን የአእምሮ ዝግጁነት በማሳደግ የማለፍ ምጣኔን ለማሻሻል ያለመ ነው።
ስልጠናው በዋናነት ተማሪዎች የፈተና ስጋትን ተቋቁመው "እችላለሁ" የሚል መንፈስ እንዲያሳድጉና በራስ መተማመናቸው እንዲጎለብት ለማስቻል ታስቦ የተዘጋጀ ነው። ይህም ተማሪዎች በፈተና ወቅት የሚገጥሟቸውን ጫናዎች ወደ ስኬት እንዲቀይሩና ለላቀ አካዳሚያዊ ውጤት እንዲዘጋጁ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥርላቸው ተገልጿል።
በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የስነ-ልቦና ትምህርት ክፍል የተመራው ስልጠና ተማሪዎች በፈተና ወቅት የሚገጥሟቸውን ጫናዎች ተቋቁመው የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ተገልጿል።
Share This News