የህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የላቀ አፈጻጻም ላሳዩ ከፍተኛ አመራሮች፣ የስራ ክፍሎች፣ ባለድርሻ አካላት፣ መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች ያዘጋጀው የእውቅና መርሃ ግብር
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የአንስቴዢያ ት/ርት ክፍል ሀገራዊ እውቅና እንዲያገኝ አበርክቶ ለነበራቸው፣ በምርምር እና ህትመት ስራዎች ላይ የላቀ አፈጻጸም ላሳዩ እንዲሁም በክረምት የህክምና በጎ ፈቃድ አገልግሎት ስራ ላይ ተሳትፎ ለነበራቸው የዩኒቨርሲቲው አመራሮች፣ መምህራን፣ ተመራማሪዎች እና አስተዳደር ሰራተኞች እውቅና ሰጥቷል፡፡እውቅናው በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች እና መምህራን ዩኒቨርሲቲው የጀመረውን ዘርፈ ብዙ የለውጥ ስራዎች እንዲያግዙ አቅም እንደሚሆን ተገልጿል፡፡
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም የእውቅና አሰጣጡን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት ዩኒቨርሲቲው ስኬታማ እንዲሁን የሁሉም መምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች አበርክቶ እጅግ አስፈላጊ ነው ያሉ ሲሆን ልዩ አፈጻጸም ያሳዩ የስራ ክፍሎችን እና አመራሮችን እውቅና የመስጠቱ ስራ የእቅድ፣ ክትትል እና ግምገማ ስራችን አንድ አካል ሆኖ በተጠናከረ መልኩ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም አክለውም የአንስቴዢያ ት/ርት ክፍል ሀገር አቀፍ እውቅና እንዲያገኝ እገዛ ላደረጉ አመራሮች እና የኮሌጁን መምህራነ እና ተመራማሪዎች ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤክስኩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር ሁሴን መሀመድ በበኩላቸው የዩኒቨርሲቲውን ዓለም አቀፍ እውቅና እንዲኖረው የሚያስችሉ የምርምር እና ህትመት ስራ እንዲሁም የማህበረሰብ አገልግሎት እና ድጋፍ ስራዎች ላይ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ በማስታወስ በተለይ በኮሌጁ ስር የሚሰጡ ትምህርቶች ሀገራዊ እና ዓለም አቀፍ እውቅና እንዲያገኙ የጀመራቸውን ስራዎች አጠናክረው እንደሚቀጥሉበት ጠቁመዋል፡፡
የአንስቴዢያ ት/ርት ክፍል ሀገር አቀፍ እውቅና እንዲያገኝ ከዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራር ጀምሮ እስከ ትምህርት ክፍል ሃላፊዎች እና መምህራን ድረስ ብዙ የተለፋበት መሆኑን ያስታወሱት ዶ/ር ሁሴን ዛሬ የተሰጠው እውቅና ለቀጣይ ስራዎች የተሻለ አፈጻጻም ይገኝ ዘንድ አቅም እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡
በእለቱ የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም እና የምርምር እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ተማም አወል መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን የአንስቴዢያ ት/ርት ክፍል ሀገራዊ እውቅና እንዲያገኝ እገዛ ላደረጉ፣ በምርምር እና ህትመት ስራዎች የላቀ አፈጻጸም ላሳዩ እንዲሁም በክረምት የህክምና በጎ አድራጎት ስራ ላይ ለተሳተፉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የስራ ክፍሎች፣ አጋር አካላት፣ መምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች የእውቅና ሰርተፊኬት ተሰጥቷል፡፡
Share This News