Logo
News Photo

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ የስራ አመራር የፋሲካ በዓልን ከተማሪዎች ጋር ማዕድ በመጋራት አከበረ

2018 / የፋሲካ በዓል በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በደማቅ መርሃ ግብሮች ታጅቦ ተከብሮ ውሏል፡፡ በአሉን ከተማሪዎች ጋር ለማክበር የዩኒቨርሲቲውን ፕሬዝዳንት / ኡባህ አደምን ጨምሮ ምክትል ፕሬዝዳንቶች በተማሪዎች መመገቢያ አዳራሽ የተገኙ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው አመራር መላውን የክርስትና እምነት ተከታይ ተማሪዎች መልካም የፋሲካ በዓል እንዲሆንላቸው መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው አመራር ተማሪዎች በበዓል ወቅት የብቸኝነት ስሜት እንዳይሰማቸው በማሰብ ታላላቅ በዓላትን ከተማሪዎች ጋር ማዕድ በመጋራት እንዲሁም ተማሪዎችን በማበረታት እንደሚያሳልፍ ይታወቃል፡፡

 

 

Share This News

Comment