Logo
News Photo

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የከተማ ግብርና ስርዓተ ትምህርት ቀረፃ ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር ማዘጋጀቱን ገለፀ፡፡

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በከተማ ግብርና የስርዓተ ትምህርት ቀረፃ ለማስጀመር ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አድርጓል።

ይህን የባለ ድርሻ አካላት ውይይት በንግግር የከፈቱት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም የአካዳምክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት እና የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ተወካይ ለውይይት ተሳታፊዎች እና ተጋባዥ እንግዶችን የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፋል፡፡ 

ዶ/ር መገርሳ ቃሲም አያይዘው ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እንደ አገር ከተያዘው ስራ አንዱ በገጠሩ አከባቢ በሚመረቱ ምርቶች ብቻ የአገሪቱን የምግብ ፍላጎት ማሟላት እንደማይቻል ገልጸዋል፡፡ ይህን የተገነዘበው ዩኒቨርሲቲው በዛሬው ዕለት የከተማ ግብርናን በማስፋፋት የተቀመጠውን የመንግሰት አቅጣጫ እውን ለማድረግ የስርዓተ ትምህርት ቀረፃ መርሀ-ግብር ይፋ አድርጓል ብሏል፡፡ 

ዶ/ር መገርሳ እያይዘው እንደገለጹት ማህበረሰባችን የተሻለ የአመጋገብ ዘዴ በአከባቢው እንዲጠቀም ማስቻል፣ የተሻለ ምርት በማምረት ከራስ አልፎ ለጎረበትና ለአከባቢው ማህበረሰብ በማቅረብ የተረጋጋ ገበያን መፍጠር አና በጓሮ አትክልቶችን በማምረት ኢኮኖሚን ማሳደግ ያስችላል ብሏል፡፡ ዩኒቨርሲቲው እንደ አገር ከተያዘው አቅጣጫ በመከተል ለዚህ የሚመጥን ፕሮገራሞችን በማስፋፋት በተፈጥሮና ኮሚፕዩተሸናል ሳይንስ ኮሌጅ የከተማ ግብርና ካሪኩለም ማቅረቡንም ዶ/ር መገርሳ አንስቷል፡፡ 

ዩኒቨርሲቲው በከተማ ግብርና በመጀመሪያ ድግሪ ስርዓተ ትምህርት ካርኩለም ነድፎ ገንቢ ሀሳቦች በማሰባሰብ በመጪው ዓመት ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅት ማድረጉንም ገልጸዋል፡፡ 

የምርምር ህትመትና ዶክመንቴሸን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር  የሆኑት  ዶ/ር መሀመድ ቃሶ Urban Agroecology Curriculum ላይ ባቀረቡት የንድፈ ሀሳብ ዶክመንት የከተማ ግብርና ለሀገር እና ለአከባቢው ማህበረሰብ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ሰፊ ገለፃ አድርጓል፡፡

ዶ/ር መሀመድ ቃሶ አያይዘው የተቀረጸው ንድፈ ሀሳብ ለተቀናጀ የከተማ ግብር፣ ለማህበራዊ እና ለኢኮኖሚያዊ ዘርፍ፣ ስነ ምህዳር ለመጠበቅ ልያሰራ በሚያስችል የተቀረጸ ፕሮግራም መሆኑን አብራርተዋል፡፡ 

ለከተማ ግብርና ሰርቶ ማሳያ የህንጻ ዲዛይን በመምህር ፍልሞና ረጋሳ ከአርክቴክቸር ትምህርት ክፍል የጽሁፍ ሰነድ ቀርቧል፡፡

በመጨረሻም በቀረቡት ሁለት ሰነዶች ላይ ከተጋባዥ እና ከተሳታፊዎች የተነሱትን ገንቢ ሀሳቦች እንደ ግብዓት እንደሚወሰድ ተገልጿል።


Share This News

Comment