Logo
News Photo

"ሰነ-ምግባርን በመገንባት ሙስናን እንከላከል" በሚል ርዕስ ለድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ መምህራን እና የአስተዳደር ሠራተኞች ስልጠና ተሰጠ፡፡

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ስልጠናውን ያዘጋጀው ሲሆን ታዋቂው የሀገራች ምሁርና የአነቃቂ ንግግሮች አቅራቢ ዶ/ር ወዳጄነህ መሃረነ መልካም ስነ-ምግባር መገንባት ላይ ትኩረት በማድረግ ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡

በዚሁ ስልጠና ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም ባስተላለፉት መልዕክት በአሁኑ ሰዓት በሀገር ደረጃ ህልውናችንን እየተፈታተኑ ከሚገኙት ችግሮች መካከል ሙስና አንዱና ዋንኛው ነው፡፡ ይህንን ለእድገታችን ማነቆ የሆነ ችግር በጊዜ መፍትሄ ካላበጀንልት መውጣት ከማንችለው የባሰ ችግር ውስጥ ይከተናል ብለዋል፡፡    

ለበርካታ ብልሹ አሰራሮች መስፈን፣ ለመልካም አስተዳደር ችግር እና  ለሙስና ተጋላጭ መጨመር አንዱና ዋንኛው መንስኤ የስነ-ምግባር ጉድለት ነው ያሉት ዶ/ር ኡባህ  መልካም ሰነምግባር መገንባት ላይ ትኩረት አድርገን በመስራት ሁላችንም የበኩላችን ድርሻ ልንወጣ ይገባናል ብለዋል፡፡

በአሁኑ ሰዓት አገልግሎት ፍለጋ ወደ የተቋማት ስንሄድ የሚገጥመን እንግልትና መጉላላት የስነ-ምግባር ጉድለት የሚያመጣው ሰው ሰራሽ ችግር ነው ያሉት ዶ/ር ኡባህ  ለተቋማችን ተልዕኮ መሳካት፣ ለራሳችን እድገት እና መልካም ስብእና ሊኖረን ይገባል ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡

በስልጠና ላይ የሙስና አይነቶች ፣ ሙስና የሚያመጣው ተጽእኖ ፣ ሙስናን እንዴት መከላከል ይቻላል በሚሉት እና መልካም ስነ-ምግባር መገንባት ላይ ትኩረት ያደረጉ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ  ለዩኒቨርሲቲው መምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች ስልጠናው ተሰጥቷል፡፡


Share This News

Comment