Logo
News Photo

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከአሊያንስ- ኢትዮ ፍራንሲስ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ፡፡

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቀደም ሲል ለመምህራን ሲሰጥ የነበረውን የፈረንሳይኛ ቋንቋ ለማስቀጠል ከአሊያንስ- ኢትዮ ፍራንሲስ ጋር የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረመ፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በአሊያንስ- ኢትዮ ፍራንሲስ የድሬዳዋ የባህልና የኪነ-ጥበብ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ሚስተር ሰርጅ ካሮል የዩኒቨርሲቲው መምህራን እና ተመራቂ ተማሪዎችን የፈረንሳይኛ ቋንቋ እንዲማሩ የሚያስችል የመግባቢያ ሰነድ ከዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶክተር ኡባህ አደም ጋር ተፈራርመዋል፡፡
የድሬዳዋ ከተማ እና የፈረንሳይ ግንኙነት ከባቡር ሃዲድ ዝርጋታ ጀምሮ የተሳሰረ እና ከእንድ ክፍለ ዘመን በላይ የዘለቀ ግንኙነት ያላቸው መሆኑን በውይይቱ ወቅት የሁለቱም ተቋማት ኃላፊዎች ያነሱት ሲሆን የነበረውን የጠነከረ ግንኙነት በተለያዩ መስኮች የተሻለ ለማድረግ ግንኙንት መጀመሩን ተናግረዋል።
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ መምህራን እና ተመራቂ ተማሪዎች የፈረንሳይኛ ቋንቋ የትምህርት እድል መሰጠቱ በቀጣይ ዩኒቨርሲቲውን በፈረንሳይ አገር ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ለማስተሳሰር የተያዘውን እቅድ ስኬታማ ለማድረግ ትልቅ እገዛ እንደሚኖረው ሚስተር ሰርጅ ካሮል ተናግረዋል፡፡
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶክተር ኡባህ አደም በበኩላቸው አሊያንስ ኢትዮ-ፍራንሲስ ለዩኒቨርሲቲው መምህራን እና ተመራቂ ተማሪዎች ለሰጠው የቋንቋ ትምህርት እድል ምስጋናቸውን አቅርበው ዩኒቨርሲቲው ያስቀመጠውን ራዕይ እና ተልዕኮ ከዳር ለማድረስ በፈረንሳይ ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር ትስስር በመፍጠር ለድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ መምህራን እና ተመራቂ ተማሪዎችን ጨምሮ የትምህርት እድል እንዲያገኙ ትስስር መፍጠር እንደሚያስፈልግ አንስተው አሊያንስ ኢትዮ-ፍራንሲስ የበኩሉን ሚና እንደሚወጣ እምነታቸው እንደሆነ ገልጸዋል።
ዶክተር ኡባህ አክለውም ተመራቂ ተማሪዎች የፈረንሳይኛ ቋንቋን መማራቸው ሰራ የመቀጠር እድል እንደሚያሰፋ ገልጸዋል፡፡

Share This News

Comment