በድሬዳዋ አስተዳደር የ1ኛና 2ኛ ደረጃ መምህራን ሲሰጥ የነበረው የዓቅም-ግንባታ ስልጠና ተጠናቀቀ።
ድሬ ዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከድሬደዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጋር በመተባበር በአስተዳደሩ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ለሚያስተምሩ መምህራን ለሁለት ቀናት የቆይ በአንግሊዘኛ ቋንቋ ላይ ያተኮረ የአቅም-ግንባታ ሥልጠና ተሰጥቷል፡፡
በሥልጠናው በ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ የእንግሊዘኛ ቋንቋ መምህራን፣ሲኒየር የእንግሊዘኛ ቋንቋ መምህራን አማካሪ ሆነው በቀጣይ በት/ቤታቸው የሚያገለግሉ መምህራን እና ማስተማሪያ ቋንቋቸው እንግሊዘኛ የሆነ (7ኛ-8ኛ ክፍል የሚያስተምሩ) መምህራን ተሳትፈዋል።
በዚህ ለሁለት ቀናት ሲሰጥ በነበረው የአቅም ግንባታ ስልጠና ላይ ቁጥራቸው ከ220 በላይ የሚሆኑ መምህራን ስልጠናውን የወሰዱ ሲሆን ስልጠናውን በዩኒቨርሲቲው የእንግሊዘኛ ቋንቋ ት/ክፍል መምህራን ሰጥተዋል።
Share This News