Logo
News Photo

"ብክለት ይብቃ ውበት ይንቃ" ሀገራዊ የአካባቢ እንክብካቤ እና ጽዳት ንቅናቄን አስመልክቶ በድሬደዋ ከተማ በተካሄደው የፅዳት ዘመቻ ላይ ድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ተሳተፈ፡፡

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ቀኑን አስመልክቶ የተዘጋጀውን የፅዳት ዘመቻ በይፋ ያስጀመሩት የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ከንቲባ የተከበሩ አቶ ሀርቢ ቡህ ለመኖሪያ ምቹ አካባቢን ለመፍጠር ሁላችንም ትልቅ ኃላፊነት አለብን፡፡

የምስራቅ አፍሪካ ትልቋ የንግድ ፣ የኢንድስትሪ እና የአገልግሎ መዕከል ለመሆን ርዕይን የሰነቀችው ድሬደዋን ውብ ፣ፅዱና አረንጓዴ ልምላሜን ለማላበስ አስተዳደሩ ምልዐተ ህዝቡን አስተባብሮ ያከናወናቸው ተግባራት ውጤታማ በመሆናቸው ተጠናክረው ይቀጥላሉ፡፡

በአለም አቀፍ ደረጃ ለ54ኛጊዜ በዩኒቨርስቲያችን ደግሞ ለ 10ኛ ጊዜ እየተከበረ ያለው የአለም የምድር ቀን ሁላችንንም ለአካባቢያችን ሁሌም ትኩረት እንድንሰጥ የሚያደርግ ነው ያሉት በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የጆግራፊና የአካባቢ  ጥናት ትምህርት ክፍል ኃላፊ መምህር ከፈለኝ ቸርነት ቀኑን አስቦ መዋል ብቻም ሳይሆን ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማድረግ ከሁላችንም ይጠበቃል፡፡

ትምህርት ክፍሉ በአደጋ ስጋት እና ተጋላጭነት፣ ከተማ ጽዳት እና ውበት፣ ተፈጥሮ ሀብት  አያያዝ እና አጠቃቀም  እንዲሁም የጂኦ ስፓሻል መረጃ ለዘላቂ ልማት በሚል በድሬዳዋና በአካባቢዋ የተለያዩ የጥናትና የምርምርም ሥራዎች መሥራቱን የትምህርት ክፍል ኃላፊው መምህር ከፈለኝ ጠቁመው በቀጣይም እነዚህ ጅምር ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡

የአለም የምድር ቀን የፊታችን ማክሰኞ ሚያዚያ 22 ቀን 2016 ዓ.ም በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ በፓናል ውይይትና በተለያዩ ዝግጅቶች ለማክብር መታቀዱን ከጆግራፊና የአካባቢ ጥናት ትምህርት ክፍል ካገኘነው መረጃ ለማወቅ ችለናል፡፡

Share This News

Comment