Logo

Event Start Date

January 25, 2024

Event End Date

January 25, 2024

Address

#ማ ስ ታ ወ ቂ ያ

በ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ለመፈተን የምዝገባ ጊዜው ጥር 08/2016 ዓ.ም ጀምሮ ጥር 15/2016 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ መጠቀሱ የሚታወሰ ነው። 


ይሁን እንጂ በተፈታኞች ጥያቄ መሰረት የምዝገባ ጊዜው እስከ ጥር 20/2016 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን እያሳወቅን ሌሎች ሁኔታዎች ግን ቀደም ሲል በተገለጸው አግባብ የሚከናወኑ መሆኑን እናሳውቃለን። 


=========================

የመውጫ ፈተና በድጋሚ ለምትፈተኑ አመልካቾች በሙሉ


ከ2015 የትምህርት ዘመን ጀምሮ በሁሉም በቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች ለእጩ ተመራቂ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና እየተሰጠ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በ2016 ዓ.ም አጋማሽ ላይ የመውጫ ፈተናን ለመፈተን በመጠባበቅ ላይ ያላችሁ ተፈታኞች በሙሉ ፈተናው ከጥር 27- የካቲት 1/2016 ዓ.ም የሚሰጥ ይሆናል፡፡ 


ስለሆነም በሐምሌ ወር 2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተናውን ተፈትናችሁ ያላለፋችሁ እና ከጥር 27 - የካቲት 1/ 2016 ዓ.ም ድረስ የመውጫ ፈተናውን በድጋሚ (Re-exam) ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ያላችሁ ተፈታኞች በሙሉ ምዝገባ የምታካሂዱትና የመፈተኛ ተቋም (የመንግስት ዩኒቨርሲቲ) የምትመርጡት ከታች በተገለጸው ማስፈንጠሪያ (Link) 

(https://exam.ethernet.edu.et) 

ስለሆነ፣ ከጥር 08 እስከ ጥር 20 2016 ዓ.ም ድረስ የምዝገባ ክፍያ 500.00 ብር በቴሌ ብር ብቻ በመክፈል መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን። 

Event Location Map

Share This Event