Logo
News Photo

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የ2015 በጀት ዓመት የሁለተኛ ሩብ አመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ግምገማ አካሄደ፡፡

ዩኒቨርሲቲው በበጀት አመቱ የሁለተኛ ሩብ አመት በአራት ዘርፎችና በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የተዘጋጀውን አፈፃፀም የዩኒቨርሲቲው ካውንስል አባላት በተገኙበት ቀርቦ የተገመገመ ሲሆን በዩኒቨርሰቲው እቅድ፣ ክትትልና፣ ግምገማ ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት በተዘጋጀው ቼክሊስት መሰረት ከሁሉም ዘርፎች የተላኩት ሪፖርቶችን ገምጋሚዎችን በመመደብ እንዲገመገሙ ተደርጎአል፡፡ በተጨማሪም የካውንስል አባላት አስተያየትና ጥያቆዎችን ለአቅራቢዎቹ በማቅረብ ማብራሪያ እና ምላሽ የተሰጠ ሲሆን ቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ አቅጣጫ በማስቀመጥ አንድ ቀን የፈጀው የአፈፃፀም ግምገማ መድረክ ተጠናቋል፡፡

Share This News

Comment