Logo
News Photo

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ፕሮግራሞቹ እውቅና እንዲያገኙ እየሰራ ነው፦የሰርቬይንግ ኢንጂነሪንግ ፕሮግራም ሀገር አቀፍ እውቅና ማግኘት የሚያስችለውን የውስጥ ግምገማ አካሂዷል

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የትምህርት ጥራትን በተግባር ለማረጋገጥና አገር አቀፍ የፕሮግራም ዕውቅና (National Accreditation) ለማግኘት የሚያስችለውን የሰርቬይንግ ኢንጂነሪንግ ፕሮግራም የውስጥ ግምገማ አውደ ጥናት በዛሬው ዕለት አካሂዷል።

በአውደ ጥናቱ መግቢያ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም እንደገለጹት ‘’ዩኒቨርሲቲው በርካታ ተቋማዊ ለውጥ እና የሪፎርም አጀንዳዎች ትግበራ ላይ ነው’’፡፡ ከእነዚህ ሀገራዊና ተቋማዊ የሪፎርም አጀንዳዎች መካከል ደግሞ የትምህርት ጥራትን በተግባር ለማረጋገጥ የሚደረገው አገር አቀፍ የፕሮግራም ዕውቅና ሥራ ዩኒቨርሲቲው በልዩ ትኩረት እየሰራበት ያለ ዋነኛው መስክ መሆኑን አብራርተዋል።

የኢንስቲትዩቱ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ግርማ ቤካ በበኩላቸው ‘’የሰርቬይንግ ኢንጂነሪንግ ፕሮግራም የውስጥ ግምገማ (Internal Evaluation) መድረክ አገር አቀፍ ዕውቅና ከመጠየቁ በፊት የተከናወኑ ሥራዎችን ለመገምገም የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል። አውደ ጥናቱ ዕውቅናውን ሙሉ በሙሉ ከማሳካት አንጻር የተሰሩ ጠንካራ ጎኖችን ለማሳደግ፣ የታዩ ጉድለቶችን በጥልቀት ለመፈተሽ እና ለሚቀጥለው የውጭ ዕውቅና ራሳቸውን በሚገባ ለማዘጋጀት የሚረዳ ወሳኝ መድረክ መሆኑንም በዝርዝር አብራርተዋል።

በዚሁ ወርክሾፕ ላይ የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ዳይሬክተር ዶ/ር አሸናፊ ተስፋዬ ለአገር አቀፍ ዕውቅና ጥያቄ መሟላት ስለሚገባቸው ደንቦችና ቅድመ-ሁኔታዎች ላይ ዝርዝር ማብራሪያና ገለጻ ሰጥተዋል።

Share This News

Comment