Logo
News Photo

1447ኛው ኢድ አል አደሀ (አረፋ) በዓል በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ዋለ:- የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች በዓሉን ከተማሪዎች ጋር አክብረዋል፡፡

1447ኛው የኢድ አል አደሃ (አረፋ) በዓል በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በደማቅ ሁኔታ እየተከበረ ይገኛል። ዩኒቨርሲቲው በዓሉን አስመልክቶ ደማቅ የምሳ ፕሮግራም ልክ እንደወትሮው ሁሉ ያዘጋጀ ሲሆን የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮችም በዓሉን ከተማሪዎች ጋር ማዕድ በመጋራት በጋራ አሳልፈዋል፡

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር መገርሳ ቃሲም፣ የአስተዳደር እና ልማት ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሰለሞን ዘሪሁን፣ መ/ር እንዳለ ሞገስ የተማሪዎች ዲን እንዲሁም የተማሪዎች ህብረት ፕሬዝዳንት እና አመራሮች በምሳ መርሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንዲሁም ሙስሊም የዩኒቨርሲቲያችን ማህበረሰብ እንኳን ለ1447ኛው ኢድ አል አደሀ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላም፣ የደስታ እና የፍቅር እንዲሆንላችሁ ልባዊ ምኞቱን ይገልፃል፡፡ 

Share This News

Comment