Logo
News Photo

ድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ከሁለተኛ ትውልድ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ቀዳሚ ተመራጭ!!

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የ2014 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና ወስደው ከ50 በመቶ በላይ በማምጣት ቀጥታ ወደ ዩኒቨርሲቲ በሚገቡ ተማሪዎች በአገራችን ከሚገኙት 45 ዩኒቨርሲቲዎች መካከል 7ኛ ተመራጭ ሆነ፡፡
የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮችና መላው የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ዩኒቨርሲቲው በተማሪዎች ተመራጭ መሆኑ ታላቅ ደስታ የሚሰማው መሆኑን እየገለፁ ለተማሪዎቹም ደማቅ አቀባበል በማድረግ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ቆይታቸው ደስተኛና ውጤታማ እንዲሆኑ አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑንም በዚሁ አጋጣሚ ለመግለፅ ይወዳል፡፡
ውድ ተማሪዎቻችን እንኳን ወደ ምስራቅ ኢትዮጵያዋ የፍቅርና የአንድነት ተምሳሌት ወደ ሆነችው የበርሀዋ ንግሰት ድሬደዋ እንኳን በደህና መጣችሁ እያልን ምርጫችሁ ለድሬደዋና ለአካባቢው እድግት የነዋሪው ህይወት መሻሻል ከመቼው ጊዜ በላይ ያልተቋረጠ ጥረትና እንቅስቃሴ እያደረገ የሚገኘው የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ በማድረጋችሁ ታላቅ ኩራት እንዲሰማን አድርጋችሁናል፡፡
በተለይም ዩኒቨርሲቲያችን በመማር ማስተማር ፣በምርምርና የምህበረሰብ አገልግልት ከመቼው ጊዜ በላይ ተሸለ ውጤት በማስመዝገብ ላይ ባለበትና ዩኒቨርስቱያችን ወደ አፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲነት የሚያደርገውን ሽግግር እያፋጠነ ባለበት ወቅት የውድ ተማሪዎቻችን ምርጫ መሆን መቻላችን ደስታችን እጥፍ ድርብ ከማድረጉም በላይ የጀመርናቸውን ተስፋ ሰጪ ተግባረት ከዳር እንድናደርስ ትልቅ አቅም የፈጠረልን መሆኑን ስንገልፅ አሁንም በታላቅ ደስታ ነው፡፡
በድጋሚ ለሁላችንም እንኳን ደስ አለን… እንኳን ደስ አላችሁ….. እያልን የዩኒቨርሲቲያችን ርዕይ ለማሳካት ሁላችንም በጋራ እንረባረብ በማለት መልዕክታችን እናስተላልፋለን….

Share This News

Comment