Logo
News Photo

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለክቡር አምባሳደር መሀሙድ ዲሪር ጌዲ የክብር ዶክትሬት አበረከተ

ዩኒቨርሲቲው ዛሬ በ15ኛው ዙር የተማሪዎች የምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ለክቡር አምባሳደር መሀሙድ ዲሪር የክብር ዶክትሬት አበርክቷል፡፡

ክቡር  አምባሳደር መሀሙድ ዲሪር ጌዲ ለአገርና ለድሬዳዋ ያበረከቱትን ታላቅ አስተዋጽዖ ከግምት ውስጥ በማስገባት የክብር ዶክትሬቱ ማበርከቱን ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል፡፡ ክቡር  አምባሳደር መሀሙድ ዲሪር ጌዲ በበኩላቸው በተወለዱበትና ባደጉበት ከተማ በሚገኘው ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት በማግኘታቸው ታላቅ ደስታ የተሰማቸው መሆኑን ተናግረዏል፡፡

Share This News

Comment