Logo
News Photo

አስደሳች ዜና ለድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሴኔት ሐምሌ 11/2015 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ለአንድ የዩኒቨርሲቲው መምህርና ተመራማሪ የማዕረግ እድገት አጽድቋል፡፡ 

የሴኔት አባላቱ ባደረጉት ስብሰባ በትምህርት ክፍል፤ ኮሌጅና በSPARC ፀድቆ የቀረበላቸውን የመምህር ደረጃ እድገት በመመርመር በተፈጥሮና ኮምፒወቴሽናል ሳይንስ ኮሌጅ የፊዚክስ ትምህርት ክፍል መምህር ለሆኑት ዶ/ር ሰለሞን ዘሪሁን ወረታ በፊዚክስ የተባባሪ ፕሮፌሰር (Associate Professor of Physics) ማዕርግ ዕድገት ሰጥቷል፡፡

መምህሩ ከመደበኛው የማስተማርና ምርምር ስራ በተጨማሪ  በተለያዩ የሃላፊነት ደረጃ በማገልገል ለዩኒቨርሲቲው ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጾ ያበረከቱ ሲሆን በአሁኑ ጊዜም የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት በመሆን እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡ 

Share This News

Comment