Logo
News Photo

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ መደበኛ ስብሰባውን ተጠናቀቀ።

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ መደበኛ ስብሰባውን ያካሄደ ሲሆን የተለያዩ ጉዳዮች ላይ በመወያየት ውሳኔ አስተላልፎአል።

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በአፕላይድ ሳይንስ ዘርፍ ብቁ እና ተወዳዳሪ የሆነ የሰው ሀይል በማፍራት፣  በምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ትኩረት አድርጎ እንዲሰራ የተጀመሩ ስራዎች እንዲጠናከሩ አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡  አዲስ በተከለሰው የዩኒቨርሲቲው መዋቅር መሠረት የምክትል ፕሬዝዳንቶች ምደባ ያከናወነ ሲሆን የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዝዳንት ቦታ ላይ ዶ/ር ሰለሞን ዘሪሁን  በሌላ በኩል የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት ዶ/ር ተማም አወል ሆነው እስካሁን በኃላፊነት የቆዩበት ጊዜ ታሳቢ ተደርጎ ቀሪ የኃላፊነት ጊዜያቸው እስኪጠናቀቅ ድረስ እንዲያገለግሉ ተመድበዋል።

በመጨረሻም የስራ አመራር ቦርዱ ለሁለቱ ም/ፕሬዝዳንቶች በቀራቸው የስራ ጊዜ መልካሙ ሁሉ እንዲገጥማቸው ተመኝተዋል።

Share This News

Comment