Logo
News Photo

በተለያዩ የንግድ ዘርፍ ላይ ከተሰማሩ አቅራቢዎች ጋር ውይይት ተካሄደ፡፡

በድሬዳዋ ራስ ሆቴል የተካሄደውን የውይይት መድረክ በንግግር የከፈቱት የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደርና ልማት ምሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር ሰለሞን ዘሪሁን መድረኩ ከዚህ ቀደም ከግዥ ጋር ተያይዞ ጎልተው የሚታዩ ችግሮች በከፍተኛ ደረጃ ለመቀነስ ታላሚ ያደረገ ነው፡፡

በተለይም መድረኩ በዩኒቨርሲቲውም ሆነ በአቅራቢ ድርጅቶቹም በኩል ግዢ ሲፈፀምና ፍያ በሚካሄድበት ወቅት ለሥራው እንቅፋት የሆኑ ቸግሮችን ነቅሶ በማውጣት ዘላቂ መፍትሔ እንዲበጅላቸው ጥርጊያ መንገድ የሚከፍት ነው ብለዋል፡፡


በመድረኩ ላይ በዩኒቨርሲቲው የግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ደረጀ ውብሸት የግዢ ሰርዓት ምንነት ፣ የግዢ ህጎች ፣የግዥ ደንብና መመሪያዎችን አስመልክቶ ገለፃ አድርገዋል፡፡


በመድረኩ ላይ ተሳታፊ ነበሩት በተለያዩ የንግድ ዘርፍ የተሠማሩ አቅራቢዎች በተለይ ከክፍያ መዘግየት ጋር የተያያዙ የነበሩ ችግሮች እንዲቀረፉ ትኩረት እንዲሰጥብት ጠይቀዋል።

ለአንድ ቀን በቆየወ የውይይት መድረክ ላይ ቁጥራቸው ከ70 ያላነሱ በድሬዳዋ የሚገኙ በተለያዩ የንግድ ዘርፎች የተሠማሩ አቅራቢዎች ተሳታፊ ሆነውበታል፡፡

Share This News

Comment