Logo
News Photo

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የበለፀገው የወንጀል ምዝገባና የመረጃ አስተዳደር ስርዓት በሐረሪ ክልል ስራ ለማስጀመር የስምምነት ሰነድ ተፈረመ ፡፡

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ  የወንጀል ምዝገባና የመረጃ አስተዳደር ስርዓት ለማበልፀግ ከሐረሪ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጋር ውል በገባው መሰረት ሶፍትዌሩን የማበልፅግ ስራ በመጠናቀቁ በክልሉ ስራ ለማስጀመር በሐረሪ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ፣በፖሊስ ኮሚሽን እና በክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ኤጀንሲ መካከል የስምምነት ሰነድ ተፈረመ፡፡

በመርሃ  ግብሩ ላይ የተገኙት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት የሆኑት  ዶ/ር ተማም አወል  የሐረሪ ክልል ጠቅላይ አቃቤ  ህግ  ዩኒቨርሲቲው ሶፍትዌሩን እንዲያበለፅግ እድል በመስጠቱ  በማመስገን፤ ሶፍትዌሩ  በልፅጎ  በክልሉ ተግባራዊ ለመሆን በመብቃቱ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል፡፡ አክለውም በሶስቱ ተቋማት መካከል የተደረሰው  ስምምነት  ክልሉን    በቴክኖሎጂ የተመራ ዘመናዊ አሰራርን ለማላበስና ቀልጣፋ አገልግሎትን ተደራሽ ለማድረግ እንደሚረዳው ገልፀው  በቀጣይም  በቴክኖሎጂ የተደገፈ ዘመናዊ አገልግሎት መስጠት የሚያስችሉ አሰራሮች እንዲኖሩ ለማድረግ  ዩኒቨርሲቲው ተገቢውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልፀዋል ፡፡

የሐረሪ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ  የተከበሩ አቶ አዩብ አህመድ  በበኩላቸው የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ  ሶፍትዌሩን በማበልፀጉ በማመስገን  ስምምነቱ የወንጀል ምርመራ ስርዓቱን በማዘመን ዜጎች በእውነታ ላይ የተመሠረተ የፍትህ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችል ነው ብለዋል። 

የሐረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ረምዚ ሱልጣን በበኩላቸው ስርዓቱ ፍትሐዊ አገልግሎት ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ያለውን ስራ በማገዝ ረገድ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልፀዋል።

Share This News

Comment