Logo
News Photo

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች መሰጠት ተጀመረ

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ለማህበራዊ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና ተፈታኞች ሀገራዊ የመልቀቂያ ፈተና መስጠት ጀምሯል። የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የሚወስዱ የማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች በሁለት ዙር ፈተናቸውን የሚወስዱ ሲሆን የመጀመሪያው ዙር የፈተና መርሃ ግብር ዛሬ ጀምሯል። 


ዛሬ የጀመረው የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና በበይነ መረብ (online) 598 እና በወረቀት የሚፈተኑ 607 በድምሩ 1205 ተማሪዎችን ያሳተፈ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል። 


የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የፈተና ስነ ምግባሮችን የጠበቀ፣ ሰላማዊ እና ምቹ የፈተና ከባቢን በመፈጠር ተማሪዎች ያለምንም ችግር እንዲፈተኑ ሰፊ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል።

Share This News

Comment