Logo
News Photo

የ2017 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና የመጀመሪያ ዙር በሰላም ተጠናቀቀ

ሰኔ 23 የጀመረው የመጀመሪያ ዙር የ12ኛ ክፍል የመልቀቂያ ፈተና በሰላም ተጠናቋል። የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ 1486 ተፈታኝ ተማሪዎችን ተቀብሎ ያስፈተነ ሲሆን ፈተናው ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተጠናቋል። ፈተናው ሰላማዊ እና ህግ እና ስርዓቱን ጠብቆ እንዲካሄድ አስተዋፅ ኦ ላደረጉ አካላት በጠቅላላ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማኔጅመንት ምስጋና አቅርቧል።
ሁለተኛው ዙር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የመልቀቂያ ፈተና ነገ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የሚጀምር ሲሆን ዩኒቨርሲቲው ተፈታኞችን ተቀብሎ ለማስተናገድ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ለማወቅ ተችሏል።

Share This News

Comment