Logo
News Photo

የ2017 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ መሰጠት ጀመረ

ሀገር አቀፉ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ መሰጠት ጀምሯል። ዛሬ በተጀመረው የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ላይ 534 በወረቀት እንዲሁም 952 ተማሪዎች ደግሞ በበይነ መረብ (online) ታግዘው ፈተና እንደሚወስዱ ታውቋል።

የፈተናውን መጀመር አስመልክቶ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም በፈተና መስጫ ቦታዎች በመገኘት የፈተና ሂደቱ መመሪያን የተከተለ እና በአግባቡ ስለመጀመሩን ማረጋገጥ ችለዋል። 

Share This News

Comment