እንኳን ደስ አለን !! እንኳን ደስ አላችሁ!!
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ 3 የምርምር ጆርናሎች ሀገር አቀፍ እውቅና አገኙ
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከ 2014 ዓ/ም ጀምሮ የተለያዩ ምርምሮችን ለተመራማሪዎች፣ ምሁራን እና ፓሊሲ አውጪዎች ተደራሽ የሚያደርግበት የምርምር ጆርናሎች ሀገር አቀፍ እውቅና አግኝተዋል፡፡
እውቅና ያገኙት 3ቱ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጆርናሎች
⏩ Harla Journal of Applied Science and Materials
⏩Harla Journal of Health and Medical Science
⏩Harla Journal of Social and Behavioral Studies
ሦስቱ የምርምር ጆርናሎች ጠንካራ የህትመት መምሪያ፣ ቋሚ የህትመት እና ስርጭት ተደራሽነት፣ የዲዛይን እና የገጽ ጥራት (layout design) ያላቸው መሆኑ በትምህርት ሚኒስቴር ታምኖበት እውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡ እውቅናው ምሁራን ምርምሮቻቸውን ለህትመት የሚያበቁበት፣ የምርምር ውጤቶች አለም አቀፍ እይታን/ ተነባቢነትን እንዲያገኙ የሚያስችል ከመሆኑም በላይ ችግር ፈቺ የምርምር ውጤቶችን፣ መረጃዎችን እና ማጣቀሻ ጽሁፎች ለአንባቢው በቀላሉ ተደራሽ እንዲሆኑ የሚያግዝ ትልቅ ስኬት ነው፡፡
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ችግር ፈቺ እንዲሁም ጭብጥ ተኮር ምርምሮችን በመስራት፣ ሀገር እና ዓለም አቀፍ የምርምር መድረኮችን በማዘጋጀት ሀገራዊ ተልዕኮውን እየተወጣ ይገኛል፡፡
Share This News