Logo
News Photo

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እና ከኢትዮጲያ ምግብ እና መድሃኒት ባለስልጣን መካከል የመግባቢያ ሰነድ ተፈረመ፡፡

በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ እና በኢትዮጲያ ምግብ እና መድሃኒት ባለስልጣን መካከል በህክምና፣ በካሪኩለም ቀረፃ እና ትግበራ፣ በግንዛቤ ማስጨበጥ ስራዎች፣ ላቦራቶሪዎችን በጋራ መጠቀም፣ በጋራ በምርምር፣ በማህበረሰብ አገልግሎት እንዲሁም በኢንተርንሺፕ እና ኤክስርንሺፕ ጉዳዮች በጋራ ለመስራት የሚያስችል ሰነድ በሁለቱ ተቋማት መካከል ተፈርሟል፡፡


በፊርማ ሰነስርዓቱ ወቅት የሁለቱም ተቋማት ተወካዮች የተገኙ ሲሆን የፊርማ ሰነድ ከማኖር ባለፈ ውጤታማ ግንኙነቶችን ከመፍጠር አኳያ ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል፡፡ በውይይቱም እንደተገለፀው ከሁለቱም ተቋማት የተውጣጡ የቴክኒክ አባላት ያሉት ቡድን የሚዋቀር ሲሆን ትብብሩን ወደተግባር የሚለውጡ እቅዶችን በማዘጋጀት ወደትግበራ በፍጥነት እንደሚገቡ ተገልፆዋል፡፡

Share This News

Comment