Logo
News Photo

ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ግማሽ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ውይይት ተደረገበት፡፡

የዩኒቨርሲቲ የ2016 ግማሽ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በየዘርፉ ቀርቦ በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጓል፡፡

በዛሬው እለት የቀረበው ሪፖርት የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ፣ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት እና የአስተዳደርና ልማት ም/ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት እንዲሁም በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በግማሽ ዓመቱ ከእቅድ አንፃር የክንውን አፈፃፀም ሪፖርት በዝርዝር ቀርቧል፡፡ 

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም እንደገለጹት መድረኩ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን በመለየት ችግሮቻችንን ለመቅረፍ ትልቅ እገዛ እንደሚኖረው ጠቁመው በግማሽ በጀት ዓመቱ የተገኙ አበረታች ውጤቶችን አጠናክረን በማስቀጠል ዩኒቨርሲቲው ተልዕኮውን በማሳካት  ርዕይውን   እውን ማድረግ እንዲችል መላው የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ርብርብ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Share This News

Comment