Logo
News Photo

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የጤና ሚኒስትር ሚኒስቴር ዲዔታ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታል የግንባታ ሂደት ጎበኙ፡፡

የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ ክቡር ሀርቢ ቡህ፣ የጤና ሚኒስትር ሚኒስቴር ዲዔታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ፣ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ተወካይ እና የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር ተማም አወል፣ የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ጽጌሬዳ ክፍሌ እንዲሁም የዩንቨርሲቲው ህክምና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አመራሮችን ያካተተ ቡድን የማስተማሪያና ሪፈራል ሆስፒታሉን ያለበትን የግንባታ ሂደት የጎበኙ ሲሆን ሆስፒታሉ በከፊል ስራ ለማስጀመር  ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ርብርብ እንዲያደርጉ አስገንዝበዋል።

Share This News

Comment