Logo
News Photo

ለድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የካውንስል አባላት የመመሪያ አዘገጃጀትን አስመልክቶ ስልጠና ተሰጠ፡፡

ስልጠናው በዋናነት የፌደራል አስተዳደር ሥነ-ሥርዓት አዋጅ ቁጥር 1183/2012ና የአስተዳደር ተቋም ረቂቅ መመሪያ ለፍትህ ሚኒስቴር ለአስተያየት የሚላክበትና የፀደቀ  መመሪያ የሚመዘገብበት የአስተዳደር ሥነ-ሥርዓት መመሪያ ቁጥር 911/2014 አዋጅን አስመልክቶ ለዩኒቨርሲተው የካውንስል አባላት ስልጠና መሰጠቱን በዩኒቨርሲቲው የስነ-ምግባርና የፀረ ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሄኖክ አየለ ተናግረዋል፡፡


የካውንስል አባላቱ ስልጠናውን መውሰዳቸው በተቋሙ ውሰጥ የሚዘጋጁ ማንኛውም መመሪያዎች ህግን ተከትለው መዘጋጀት እንዲችሉ ትልቅ እገዛ ያደርጋል በማለት አቶ ሄኖክ አብራርተዋል፡፡

Share This News

Comment