Logo
News Photo

ሂውማን ብሪጅ የተሰኘ ግብረሰናይ ድርጅት ለድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያና የህክምና ሆስፒታል የሚውሉ የህክምና መሣሪያዎች ድጋፍ ለማድረግ ከዩኒቨርሲቲው ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡

የመግባቢያ ሰነዱን በዩኒቨርሲቲው በኩል የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም በሂዩማን ብሪጅ በኩል ደግሞ የድርጅቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አዳሙ አንለይ ፈርመዋል፡፡

በስምምነቱ መሠረት ግብረሰናይ ድርጅቱ ለድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ማስተማሪያና የህክምና ሆስፒታል የተለያዩ የህክምና መገልገያ መሣሪያዎችንና የሆስፒታል የመኝታ አልጋዎች ድጋፍን የሚደርግ መሆኑ በስምምነቱ ወቅት ተገልፃል።


ሂዩማን ብሪጅ የተሰኘውና መሠረቱን ስዊድን ሀገር ያደረገው ግብረሰናይ ድርጅት ከዚህ ቀደም ለድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ዘመናዊ ከፍተኛ ክሊኒክ የህክምና መገልገያ መሣሪያዎችና የሆስፒታል የመኝታ አልጋዎች ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

Share This News

Comment