Logo
News Photo

በ8ኛው ዙር ሀገር አቀፍ የምስለ ችሎት ውድድር የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ  4 ዋንጫዎችን በማግኘት አሸናፊ ሆነ፡፡

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በሚገኘው በአሶሳ ዩኒቨርሲቲ  አዘጋጅነት  በ 31 ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ሲካሔድ በነበረው  በ8ኛው ዙር ሀገር አቀፍ የምስለ ችሎት ውድድር ላይ የድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ  4 ዋንጫዎችን በማግኘት ውድድሩን በአንደኝነት አሸንፏል።

በውድድሩ ላይ ተማሪ ምህረት ወንድሙ ፣ ተማሪ ማህሌት ወርቅነህ እና ተማሪ ሰብለ ገሰሰ አሻናፊ በመሆን የዋንጫና የሜዳሊያ ተሸለሚ ሆነዋል ፡፡

በ8ኛው ዙር አሸናፊ ለሆኑ ተማሪዎችና ለተማሪዎቹ አሰልጣኝ መምህር አለምሰገድ ደጀኔ የዩኒቨርሲቲያችን አመርራሮች፣  የህግ ኮሌጅ መምህራን እና ተማሪዎች በድሬዳዋ አለም ኤርፖርት በመገኘት ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

Share This News

Comment