የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር የተገነባው የዲጂታል ትምህርት መስጫ መልቲሚዲያ ስቱዲዮ ተመረቀ፡፡
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
በሀገራችን ኢትዮጵያ በሚገኙ በተመረጡ 5 የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የዲጂታል የትምህርት ስርዓትን ለመዘርጋት ተግባረዊ እየተደረገ ያለው ፕሮጀክት (e-SHE) /e-Learning for Strengthening Higher Education / ይሰኛል፡፡
ፕሮጀክቱም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የትምህርት ሚኒስቴር ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን/Mastercard Foundation፣ ከአሪዞና ስቴት ዩኒቨርሲቲ፣ ከሻያሾኔ እና ከ50ዎቹ ዩኒቨርሲቲዎች በትብብር ካለፈው 2 ዓመት ወዲህ ተግባራዊ ሲያደርግ የቆየ ነው፡፡
በዛሬው እለትም የዚሁ ፕሮጀክት አንድ አካል የሆነው በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የተገነባው የዲጂታል መልቲሚዲያ ስቱዲዮ በይፈ ተመርቋል፡፡
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ኡባህ አደም የ (e-SHE) ፕሮጀክት በምስራቁ ክላስትር ስር የታቀፉትን 5 ዩኒቨርሲቲዎችን የመማር ማስታማር ተልዕኳቸውን በማዘመን ወደፊት አንድ እርምጃ የሚያራምድ ዲጂታል መልቲሚዲያ ስቲዲዮ ነው ብለዋል፡፡
በአሁኑ ሰዓት የዲጂታል ትምህርትን ለማስጀመር አስፈላጊ ተግባራት ተከናውነው ጥቂት ስወራዎች ብቻ መቅረታቸውን ጠቁመዋል፡፡
ፕሮጀክቱ ከዚህ በበለጠ እንደ ሀገር ዲጂታላይዜሽን ከባቢን ለመፍጠር የተጀመረውን ጉዞ ከዳር ለማድረደስ በዩኒቨርሲቲው የተገነባው በዲጂታላይዜሽን ቴክኖሎጂ የሚመራው ትምህርት መሠረት ሆኖ ጥሩ መደላድል የሚፈጥር መሆኑን በምራቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተናግረው ለፕሮጀክቱ እዚህ ደረጃ ላይ መድረስ የራሳቸው አስተዋፅዖ ለነበራቸው አካላትና ግለሰቦች ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
ከምረቃው ስነ-ስርዓት ቀደም ብሎ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ጨምሮ በክላስተር በአንድ ላይ እንዲታቀፉ የተደረጉት 5ቱ (ሃረማያ ፣ ጅግጅጋ ፣ቀብሪዳህር እና ኦዳቡልቱም ) ዩኒቨርሲቲዎች ተወካይ የሆኑ የጋራ ውይይት አካሂደዋል፡፡
በዚሁ የውይይት መድረክ ላይ ይሄንን ፕሮጀክት በሚከውነው የሻያሾኔ ድርጅት የe-SHE ፕሮጀክት ማናጀር የሆኑት ወ/ሮ መክሊት ምንተስኖት እንደገለጹት በአሁኑ ሰዓት ከፖሊሲ፣ ከመሠረተ-ልማት፣ ከዲጂታል ሲስተም እና የመምህራን አቅም ከመገንባት አንፃር ብዙ ርቀት ያስጓዙ ተግባራትን መፈፀም ተችሏል፡፡ በአሁኑ ሰዓትም በ50ዎቹ ዩኒቨርሲቲዎች የዲጂታል ትምህርቱን ለማስጀመር እገዛ የሚያደርጉ መመሪያዎች ተዘጋጅተው መበተናቸውን ወ/ሮ መክሊት ተናግረዋል፡፡
በዛሬው እለት በድሬዳዋ የሚገኘውን ዲጂታል መልቲሚዲያ ስቱዲዮን ጨምሮ e-SHE ፕሮጀክቱን ተግባራዊ ባደረገባቸው 5 ዩኒቨርሲቲዎች የዲጂታል መልቲሚዲያ ስቱዲዮዎች በይፋ ተመርቀው ርክክብ ተደርጎባቸዋል፡፡
ዛሬ በድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ በኢ-ሺ ፕሮጀክት የተመረቀው የዲጂታል መልቲሚዲያ ስቱዲዮ ድሬደዋ ዩኒቨርሲቲ መዕከል ሆኖ 5 የምስራቁ አካባቢ ዩኒቨርሲቲን (ሃረማያ ፣ ጅግጅጋ ፣ቀብሪዳህር እና ኦዳቡልቱም ) በክላስትር ታቅፈው የሚጠቀሙብት ሲሆን 35 ሺህ መምህራን ለማሰልጠን እቅድ ተይዞ 8 መቶሺህ ተማሪዎች ተጠቃሚ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
Share This News