Logo
News Photo

የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ ከዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ጋር ውይይት እና የ9 ወር የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ።

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር እና ዩኒቨርሲቲው የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ክብርት ዶ/ር ፍፁም አሰፋ በተገኙበት የዩኒቨርሲቲውን መማር ማስተማር፣ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት እና መልካም አስተዳደር ዙሪያ ከዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ጋር ውይይት የተደረገ ሲሆን ለዩንቨርሲቲው የስራ አመራር ቦርድ የ9 ወር የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦላቸው ውይይት ተደርጎበታል።

በመጨረሻም ክብርት ሚኒስትር ዶ/ር ፍፁም አሰፋን ጨምሮ የቦርዱ አባላት በቅርቡ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ በይፋ የተመረቀውን የኢ-ለርኒንግ ዲጂታል መልቲሚዲያ ስቱዲዮ ጎብኝተዋል፡፡

Share This News

Comment